Lyrics
ብቸኝነቴን ነው እኔ ማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታሁኝ ድንገት ሳላስበው
ብቸኝነቴን ነው እኔ ማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታሁኝ ድንገት ሳላስበው
ሲጀምሩት ፍቅር እንዴት ይጣፍጣል
እስካገኘው ድረስ መንፈሴ ይረበሻል
እንዲያ እንደወደድኳት እዘልቀው ይሆን
እንጃልኝ ፈራሁኝ ጠረጠርኩ እሷን
እንጃልኝ ፈራሁኝ ጠረጠርኩ እሷን
ብቸኝነቴን ነው እኔ ማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታሁኝ ድንገት ሳላስበው
ብቸኝነቴን ነው እኔ ማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታሁኝ ድንገት ሳላስበው
ሳላያት ከዋልኩኝ ጊዜው ሲረዝምብኝ
አግኝቺያትም መጥገብ በፍፁም አቃተኝ
ከሷ ጋር ስጫወት ቀኑ እያጠረብኝ
ምነው ሰዐቱ ለኔ በሆነልኝ
ምነው ሰዐቱ ለኔ በሆነልኝ
ብቸኝነቴን ነው እኔ ማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታሁኝ ድንገት ሳላስበው
ብቸኝነቴን ነው እኔ ማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታሁኝ ድንገት ሳላስበው
መጨረሻውን እንጃ የፍቅራችን ወሰን
ይጠፋል ይለማል እንዴት ይሆን ይሆን
ጉጉቴ ብዙ ነው ለማየት ፍቅራችን
እድሜ እንለምናለን ለኔም ለሷም ሚሆን
እድሜ እንለምናለን ለኔም ለሷም ሚሆን
እድሜ እንለምናለን ለኔም ለሷም ሚሆን
እድሜ እንለምናለን ለኔም ለሷም ሚሆን
እድሜ እንለምናለን ለኔም ለሷም ሚሆን
እድሜ እንለምናለን ለኔም ለሷም ሚሆን