Lyrics
ዝም ስል እንዳይከፋኝ አፅናንተሽ
ላትከጂኝ ላትለይኝ ቃል ገብተሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
ዝም ስል እንዳይከፋኝ አፅናንተሽ
ላትከጂኝ ላትለይኝ ቃል ገብተሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
ከ'ንግዲህ ላልጨነቅ ላይከፋኝ
የሚደንቀኝ ፅኑነትሽ አኮራኝ
የእውነት ልቤ ገብተሽ ነግሠሻል
ልንገርሽ በቃል ኪዳን ፀንተሻል
ሳላይሽ ውዬ አላድርም ታውቂያለሽ
አምላክም መልካም አርጎ ፈጠረሽ
ሳላይሽ ውዬ አላድርም ታውቂያለሽ
አምላክም መልካም አርጎ ፈጠረሽ
ጌጤ ቤቴ መስታወቴ
መኩሪያዬ ነይ ስስቴ
ጥንቅር ብሎ ለምን አይቀር
ካንቺ አይበልጥም ሁሉም ነገር
ጌጤ ቤቴ መስታወቴ
መኩሪያዬ ነይ ስስቴ
ጥንቅር ብሎ ለምን አይቀር
ካንቺ አይበልጥም ሁሉም ነገር
ዝም ስል እንዳይከፋኝ አፅናንተሽ
ላትከጂኝ ላትለይኝ ቃል ገብተሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
ዝም ስል እንዳይከፋኝ አፅናንተሽ
ላትከጂኝ ላትለይኝ ቃል ገብተሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
የእውነት የፍቅር ቃል አንቺው ነሽ
የሆዴን የምታውቂ ሚስጥሬን
ልናገር እስኪ ይውጣልኝ ማፍቀሬን
ላጥብቀው እንዳይላላ ማህተቤ
ታውቂያለሽ በደንብ አድርገሽ የልቤን
ሁልጊዜ ላልኖርበት በዚህ አለም
ታምኜ እኖራለሁ ለዘላለም
ሁልጊዜ ላልኖርበት በዚህ አለም
ታምኜ እኖራለሁ ለዘላለም
ጌጤ ቤቴ መስታወቴ
መኩሪያዬ ነይ ስስቴ
ጥንቅር ብሎ ለምን አይቀር
ካንቺ አይበልጥም ሁሉም ነገር
ጌጤ ቤቴ መስታወቴ
መኩሪያዬ ነይ ስስቴ
ጥንቅር ብሎ ለምን አይቀር
ካንቺ አይበልጥም ሁሉም ነገር
ከ'ንግዲህ ላልጨነቅ ላይከፋኝ
የሚደንቀኝ ፅኑነትሽ አኮራኝ
የእውነት ልቤ ገብተሽ ነግሰሻል
ልንገርሽ በቃል ኪዳን ፀንተሻል
ሁልጊዜ ላልኖርበት በዚህ አለም
ታምኜ እኖራለሁ ለዘላለም
ሁልጊዜ ላልኖርበት በዚህ አለም
ታምኜ እኖራለሁ ለዘላለም