Lyrics

ያቀራርባል በጣም ያቀራርባል
ያቀራርባል በጣም ያቀራርባል
መልካም ፈገግታዋ ፍቅር ይመግባል
ያቀራርባል ግሩም ጨዋታዋ ከሰው ያግባባል
ያቀራርባል

ቀልድሽ ጨዋታሽ ይደምቅልሻል
ቁምነገርሽም ይሰማልሻል
አቀራረቡን ታውቂበታለሽ
አብረሽም ሆነሽ ትናፈቅያለሽ

Lyrics continue below...

Don't want to see ads? Upgrade Now

ስትጀምሪ ጨዋታ
ሊጎብዝ ነው ፈገግታ
የደከመው በረታ
ስትጀምሪ ጨዋታ
ሊጎብዝ ነው ፈገግታ
የደከመው በረታ

አይ ገንዘብሽ ነው ጨዋታ
ንብረትሽ ነው እስክስታ
ያምርብሻል ዳንኪራ
ያንቺ ጌጥ ነው ጭፈራ

ስትጀምሪ ጨዋታ
ሊጎብዝ ነው ፈገግታ
የደከመው በረታ

በይ ጥርስሽን ሳቂበት ሳቂበት
አንድም በፍቅር ጣይበት (ታውቂበታለሽ)
ባይኖችሽም ጥቀሺ ጥቀሺ
ያንቀላፋውንም ቀስቅሺ (ታውቂበታለሽ)
በይ ዳሌሽን ነቅንቂው ነቅንቂው
ቤቱንም ጨፍረሽ አድምቂው (ታውቂበታለሽ)
በይ ሽንጥሽን ምዘዢው ምዘዢው
ፍጥረተ አለሙን አፍዝዢው (ታውቂበታለሽ)

አቤት አቤት ሌላ ነው ሌላ
ጨዋታሽ ሌላ
ጭፈራሽ ሌላ
አቤት አቤት ሌላ ነው ሌላ
ጨዋታሽ ሌላ
ጭፈራሽ ሌላ
አቤት አቤት ሌላ ነው ሌላ
ቀልድሽ ይደምቃል
ሳቅሽ ይሞቃል
ሌላ ነው ሌላ

አይንሽ ሌላ (ሌላ)
ጥርስሽ ሌላ (ሌላ)
ፀጉርሽ ሌላ (ሌላ)
ውበትሽ ሌላ (ሌላ)
ፍቅርሽ ሌላ (ሌላ)
ቀልድሽ ሌላ (ሌላ)
ሳቅሽ ሌላ (ሌላ)
ድምፅሽ ሌላ (ሌላ)
ሁሉም ሌላ (ሌላ)

ያነጋግራል ይሄስ ያነጋግራል
ያነጋግራል ይሄስ ያነጋግራል
አይንሽ ቋንቋ አለው በፍቅር ያዋራል
ልብ ይሰብራል
የሳቅሽ ዜማ ይመግባል ያነጋግራል

ወፍ የሚያረግፍ ድምፅሽ ዜመኛ
የሚበረግግ አይንሽ ጦረኛ
ጎሽ የሚያላምድ ልብሽ ዘዴኛ
ሁሉ በእጇ ነሽ ድንቅ እድለኛ

ቢመሻሽም ሰዐቱ
አንቺ ካለሽ በቤቱ
ምን ሊጠቅም መብራቱ
ቢመሻሽም ሰዐቱ
አንቺ ካለሽ በቤቱ
ምን ሊጠቅም መብራቱ

አይ ፀሀይ ጨረር ፈንጥቃ
ኮከብ ከፍቷት ጨረቃ
አሸብረቀው ቢደምቁም
አስንቀውሽ አያውቁም

ቢመሻሽም ሰዐቱ
አንቺ ካለሽ በቤቱ
ምን ሊጠቅም መብራቱ

በይ ሳቅሽን መግቢው መግቢው
ሁሉን በዙሪያሽ ሰብስቢው (ታውቂበታለሽ)
ታጫወቺ ይደሰት በቀልድሽ
የሰማሽ ሁሉ ይውደድሽ (ታውቂበታለሽ)
ተጫወቺ አሳይን ጭፈራ
ባንቺ ላይ ያምራል ዳንኪራ (ታውቂበታለሽ)
በእጆችሽ ደባብሺው ደባብሺው
የታመመውን ፈውሺው

አቤት አቤት ሌላ ነው ሌላ
ጨዋታሽ ሌላ
ጭፈራሽ ሌላ
አቤት አቤት ሌላ ነው ሌላ
ጨዋታሽ ሌላ
ጭፈራሽ ሌላ
አቤት አቤት ሌላ ነው ሌላ
ቀልድሽ ይደምቃል
ሳቅሽ ይሞቃል
ሌላ ነው ሌላ

አይንሽ ሌላ (ሌላ)
ጥርስሽ ሌላ (ሌላ)
ፀጉርሽ ሌላ (ሌላ)
ውበትሽ ሌላ (ሌላ)
ፍቅርሽ ሌላ (ሌላ)
ቀልድሽ ሌላ (ሌላ)
ሳቅሽ ሌላ (ሌላ)
ድምፅሽ ሌላ (ሌላ)
ሁሉም ሌላ (ሌላ)

ኮላ ተላ ተማ ኔ ቱማ
ነይኔ ዱማ ነይኔ ዱማ
ኮላ ተላ ተማ ኔ ቱማ
ነይኔ ዱማ ነይኔ ዱማ

Writer(s): Tsehaye Yohannes

Don't want to see ads? Upgrade Now

API Calls

Scrobble from Spotify?

Connect your Spotify account to your Last.fm account and scrobble everything you listen to, from any Spotify app on any device or platform.

Connect to Spotify

Dismiss