Lyrics

ካ'ንዱ አንዱ ቤት
እግርሽ ይራመዳል
እኔስ አላወቅኩት
ለካ እንዲህ ኖረሻል
አየሁት ለየሁት
ገባኝ ያንቺ ባህሪ
ልብሽም አይረጋም
እንዳሻው ነዋሪ
አይንሽ ሲመለከት
ሁሉ ብርቅሽ ላንቺ
ይቅርብሽ ተሻሻይ
የኔን ምክር እንቺ
እኔ እንዳንቺ አይደለሁ
ሁሉ አይደለም ብርቄ
አልቃና ብሎኛል
ፀባይሽን አውቄ
ካ'ንዱ አንዱ ቤት
እግርሽ ይራመዳል
እኔስ አላወቅኩት
ለካ እንዲህ ኖረሻል
አየሁት ለየሁት
ገባኝ ያንቺ ባህሪ
ልብሽ የማይረጋ
እንዳሻው ነዋሪ
ለካስ እንደዚህ ነሽ
ግሩም ነው ይደንቃል
ያኳኋንሽ ነገር
ለሚያይሽ ይገርማል
ይህ ሁሉ ፀባይሽ
እኔን ሳይገባኝ
ሳላውቀው ከርሜ
ገና አሁን ታየኝ
ካ'ንዱ አንዱ ቤት
እግርሽ ይራመዳል
እኔስ አላወቅኩት
ለካ እንዲህ ኖረሻል
አየሁት ለየሁት
ገባኝ ያንቺ ባህሪ
ልብሽ የማይረጋ
እንዳሻው ነዋሪ
ላላላላላ

Writer(s): Lemma Demissew

Don't want to see ads? Upgrade Now

API Calls

Scrobble from Spotify?

Connect your Spotify account to your Last.fm account and scrobble everything you listen to, from any Spotify app on any device or platform.

Connect to Spotify

Dismiss