Lyrics

ሌላ ማየቴንም ትቼ
ባ'ንድ አንቺ ፀንቼ
የልብ እምነት ሰጥቼሽ
የትም አልሄድ ከ'ጅሽ
መብራት ብርሃኔ
አንቺው ነሽ ለኔ
አላውቅ ረስቼሽ
ለአፍታ ዘንግቼሽ
ብትሄጅም ካ'ድማስ ማዶ ርቀሽ ካ'ገር ወገን
አለብኝ ያ'ደራ ቃል ለፍቅርሽ የመታመን
ብትርቂም ካ'ጠገቤ
መቼ ሆንኩኝ እንደልቤ
አለሁ እኔ ተሰብስቤ
አንቺ ነሽ እና ረሀቤ
ስላ'ንቺ ደህንነትም ስለ'ኔም አስባለሁ
ልጠብቅ እስክትመጪ መታገስ እችላለሁ
አይደል እንኳን የሚጠሙት
እንደ እህል የሚራቡት
አይደላ አይመቺ
ሁሉ ሴት ለኔ እንዳ'ንቺ
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
አለሁ በይኝ እቱ አለሁ በይኝ
አለሁ በይኝ እቴ አለሁ በይኝ
አለሁ በይው እቱ አለሁ በይው
አለሁ በይኝ እቴ አለሁ በይኝ
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
ልቤ የለው ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
ሌላ ማየቴንም ትቼ
ባ'ንድ አንቺ ፀንቼ
የልብ እምነት ሰጥቼሽ
የትም አልሄድ ከ'ጅሽ
መብራት ብርሃኔ
አንቺው ነሽ ለኔ
አላውቅ ረስቼሽ
ለአፍታ ዘንግቼሽ
በናፍቆት ተብሰልስዬ ተክዤ ሳነሳሳሽ
ባይተዋር ብቸኛ ነኝ ዘዴ አላውቅ እንዴት ልርሳሽ
ቀን በውኔ ሌቱን በህልሜ
አልድንም ከማለሜ
ጠርጥሬሽስ መች አውቃለሁ
ብትርቂኝም አምንሻለሁ
ሺህ ቆንጆ ቢደረደር አይማርክ አይስበኝ
መች ቀላል ያንቺ ፍቅር እግሬንም አይመራኝ
ጉልበቴንም አርዶኛል
መቼ ዘና ያደርገኛል
ሳሉ በሙሉ ህዋሶቼ
አይሹም ያላንቺ መቼም
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
አለሁ በይኝ እቱ አለሁ በይኝ
አለሁ በይኝ እቴ አለሁ በይኝ
አለሁ በይው እቱ አለሁ በይው
አለሁ በይኝ እቴ አለሁ በይኝ
አለሁ በይኝ እቱ አለሁ በይኝ
አለሁ በይኝ እቴ አለሁ በይኝ
አለሁ በይው እቱ አለሁ በይው
አለሁ በይኝ እቴ አለሁ በይኝ
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው
ውዴ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ
የለውም ሌላ ሰው
ሀሳቡ ላንቺው ነው

Writer(s): Binyamir Ahmed

Don't want to see ads? Upgrade Now

API Calls

Scrobble from Spotify?

Connect your Spotify account to your Last.fm account and scrobble everything you listen to, from any Spotify app on any device or platform.

Connect to Spotify

Dismiss